በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ

Abiy Ahmed Ali (PhD)

Abiy Ahmed Ali (PhD)

47,676 views

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ፤  ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሰፊውን የምሥራቅ አፍሪካና አጠቃላይ የአፍሪካ ገበያን የማገልገል አቅም አለው።
‎በአፍሪካ ውስጥ ዓለም አቀፍ ተዓማኒነት ያለው የማጣራትና የፍተሻ አገልግሎት በመስጠት፤ ጎረቤት ሀገራትና በቀጣናው የሚገኙ የማዕድን ኩባንያዎች ወርቃቸውን ከአህጉሪቱ ውጭ መላክ ሳያስፈልጋቸው፤ ለላቀ ማጣራት፣ ለዕውቅና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፣ ለተጨማሪ እሴትና ለሽያጭ ወደ ኢትዮጵያ እንዲያመጡ ያስችላል።

The National Precious Metals Refinery, constructed within the Bole Lemi Special Economic Zone, has the capacity to serve not only Ethiopia but also the broader East African and pan-African markets. By providing internationally credible refining and testing services, it enables neighboring countries and regional mining companies to bring their gold to Ethiopia for advanced refining, certification, value addition, and sale, eliminating the need to export it outside the continent.